ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በከተማ አስተዳደሩ ተቀባይነት እንዳላገኘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ የከንቲባ ፅ/ቤት አስተዳደር ጉዳዩች ዘርፍ ጥር 18 ቀን 2013 ዓ/ም በቁጥር አ/አከፀ 18 /03/ 128 ለባልደረሳስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በፃፈው ደብዳቤ ሰልፉ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ተቀባይነት እንዳላገኘ ምላሽ የሰጠ ሲሆን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንም በግልባጭ አሳውቋል።
የተጠራው ሰልፍ ተቀባይነት ባያገኝም ጥር 23 ቀን 2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች መልእክት እየተላለፈ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።
ተቀባይነት ያላገኘ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውሶ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉም ሆነ መረጃውን እያሰራጩ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ኮሚሽኑ አሳስቧል።
የፖሊስን መልዕክት ተላልፈው ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት ላይ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
Comments
Post a Comment