ብሔራዊ ጀግና አክቲቪስት መምህር የማነ ንጉሰ ጀግናው በከሃዲዎች ተቀጠፈ - የትግራይ PP

ብሔራዊ ጀግና አክቲቪስት መምህር የማነ ንጉሰ ጀግናው በከሃዲዎች ተቀጠፈ - የትግራይ PP





የፈንቅል ሊቀመንበር የነበረው የማነ ንጉሴ በጁንታው ርዝራዥ ታጣቂዎች ተገደለ። መምህር የማነ እና ሁለት አብረውት የነበሩ የመከላከያ አባላትም ተገድለዋል። የማነ እና አብረውት የነበሩት የመከላከያ አባላት ዛሬ ከስአት ከመቐለ በቅርብ ርቀት የምትገኘው በሒዋነ ከተማ በጁንታው ርዝራዥ ታጣቂዎች ተገደለ።





መምህር የማነ ህወሓትን በመታገል ትልቅ አስተዋፅኦ የነበረው ደፋር ታጋይ ነበር። የማነ ጁንታው ከወደቀ በኋላ ህዝቡን ለማገልገል የሰብኣዊ ድጋፍ ስራ ለመስራት ህዝቡ እርዳታ እንዲደርሰው እየሰራ ፣ አንቡላንስ ያጡ ነፍሰጡር እናቶች የግለሰብ መኪና በመለመን ወደ ህክምና በማድረስ ህዝባዊ አገልግሎት ሲሰጥ ነበር።





ዛሬም ወደ ሒዋነ ይሄ ሰብኣዊ ስራ ለመስራት እየሄደ እያለ በድንገት በጁንታው ርዝራዥ ታጣቂዎች ተገድሏል። የቀብር ስነስርአቱ መቼ እንደሚፈፀም ተከታትለን ይዘን እንቀርባለን! የማነ ከልብ ደፋር ታጋይ ነበር!





ነብስህ በገነት ያኑርልን !

Comments