በአማራ ክልል ጥቃት ሲፈጸም የጸጥታ መዋቅሩ አስቀድሞ ሊያውቅና ሊከላከል ያልቻለበት ምክንያት እየተመረመረ ነው - አቶ አገኘሁ ተሻገር
ሰሞኑን በአማራ ክልል ጥቃት ሲፈጸም የጸጥታ መዋቅሩ አስቀድሞ ሊያውቅና ሊከላከል ያልቻለበትን ምክንያት እየመረመረ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ገልጸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ጉዳዩን አስመልክተው ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም በጥፋቱ አመራሮች መሳተፋቸው ጥቆማ ስለመጣ የማጣራት ስራው እየተከናወነ ነው ብለዋል።
ማንነትን መሰረት ባደረጉት ጥቃቶች የደረሰው የጉዳት መጠንም በቀጣይ ይፋ ይደረጋል ነው ያሉት።
ጥቃቱን ተከትሎ በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎች ከጥቂት ጉድለቶቻቸው በቀር የአማራን ህዝብ ክብር የመጠኑና ጨዋነትን የተላበስሱ እንደነበሩም ነው ርዕሰ መስተዳደርሩ በመግለጫቸው ያስረዱት።
ሰልፎቹ ላይ የተሳሳተ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ጥረት መደረጉንና በዛሬው ዕለትም በባህርዳር ዝርፊያ እና የንግድ አገልግሎት የመዝጋት ሙከራዎች መደረጋቸውን ተናግረዋል።
የባህርዳር ወጣቶች ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በትብብር በመስራቱ የከተማዋ እንቅስቃሴ ወደነበረበት መመለሱንም ገልጸዋል፡፡
ጥቃቱ በሠለጠና በተደራጀ ኃይል የተፈጸመ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ አካባቢውን ወደ ነበረበት ለመመለስ በተሠራው ስራ አሁን ላይ የተረጋጋ ሁኔታ መፈጠሩን በመግለጫቸው አስረድተዋል።
Comments
Post a Comment