“ኦሮሙማ የኦሮሞ ማንነት መሰረት ነዉ - Tabor Wami
በእዉቁ የታሪክ ምሁር በአቶ ታቦር ዋሚ “የኦሮሞ ማንነት እና ታሪኩ” በሚል ርዕስ የተጻፈ የታሪክ መጽሃፍ ዛሬ ይመረቃል፡፡ መጽሃፉ በ684 ገጾች የተቀነበበ ሲሆን በዋናነት የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ያለዉን ታላቅ ሚና በስፋት ያወሳል፡፡ በመጽሃፉ የኦሮሞ ህዝብ ማንነት (ኦሮሙማ)፣ የኦሮሞ የገዳ ስርዓት፣ በኦሮሞ ህብረተሰብ ዘንድ የዉትድርና ሚና፣ በኢትዮጵያ የተካሄዱ ትላልቅ ጦርነቶችና የኦሮሞ ጀግኖች ተሳትፎን፣ በኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በማህበራዊ ጉዳዮች የኦሮሞ ህዝብን ሚና በስፋት እና በጥልቀት ይዳስሳል፡፡
በመጽሃፉ በኢትዮጵያ በተደረጉ አዉደ ዉጊያዎች፣ የራስ ጎበና ዳጬ፣የራስ ወልደሚካኤል ጉዲና፣ የፊታዉራሪ ገበየሁ ጉርሙ፣ የዳጃዝማች ባልቻ ሰፎ፣ የቁሴ ዲነግዴ፣ የደጃዝማች ገብረማሪያም፣ የወረጃረሶዉ አቢቹ፣ የደጃዝማች ገረሱ Dhuኪ፣ የራስ አበበ አረጋይ፣ ሜጀር ጀነራል ጃጋማ ኬሎ፣ ደጃዝማች በቀለ ወያ፣ኮሎኔል አብዲሳ አጋ ደጃዝማች ገነነ በdhaኔ ፣ ፊታዉራሪ ጅማ ሰንበቴ፣ ሜጀር ጀነራል ሙሉጌታ ቡሊ፣ ሜጀር ጀነራል ደምሴ ቡልቶ፣ ሜጀር ጀነራል መርዕድ ንጉሴ እና የሌሎችም የጀግንነት፣ የጦር ሜዳ ዉሎ እና ለኢትዮጵያ አንድነት የከፈሉት መስዋዕትነት በዝርዝር ቀርቧል፡፡
በማህበራዊ ዘርፍ በስነ ጽሁፍ፣ በስነ ጥበብ በሙዚቃ የ እን ገብረ ክስርቶስ ደስታ ነገዎ፣ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን፣ አለቃ ተክለየሱስ ዋቅጅራ፣ ጥላሁን ገሰሰ፣ አሊ ቢራ፣ ኮሎኔል ሳህሌ ደጋጎ፣
በስፖርት ዘርፍ ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ፣ ሻምበል አበበ ቢቂላ ሻምበል ማሞ ወልዴ፣ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ፣ አትሌት ጌጤ ዋሚ፣አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ የአትሌት መሰረት ደፋር የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ከፍ ብሎ እንዲዉለበለብ፣ የኢትዮጵያ ክብር በአለም አደባባይ ከፍ እንዲል ያደረጉትን ተጋድሎ እና አበርክቶ ይዘክራል፡፡
ለህዝቦች ነጻነት እና እኩልነት የታገሉ እነ ጀነራል ታደሰ ብሩ፣ የመቶ አለቃ ማሞ መዘምር፣ ኮሎኔል አለሙ ቅጤሳ፣ ጀነራል ዋቆ ጉቱ ፣ ሃይለማሪያም ገመዳ ፣ መገርሳ በሪ፣ ሃይሌ ፊዳ፣ ነdhii ገመዳ፣ አገሪ ቱሉ፣ባሮ ቱምሳ፣ ዘዉገ ቦጂኣከ፣ ከበደ ብዙነሽ፣ኤሌሞ ቂልጡ፣ ጃራ አባ ገዳ ሃጂ አደም ሳዶ፣ሲሳይ ኢብሳ፣ ሼክ በክሪ ሳጳሎ፣ ጉተማ ሀዋስ፣ አቡነ ጴጥሮስ (መገርሳ በdhaaሳ)፣ ኦነስሞስ ነሲብ፣ አስቴር ገኖ፣ ቄስ ጉዲና ቱመሳ እና የበርካታ ጀግኖች ያልተነገሩ ገድሎችን ያነሳል፡፡
መጽሃፉ ስለ ኦሮሙማ (ኦሮሞነት፣ Oromoness) እንዲህ ይላል
…“ኦሮሙማ የኦሮሞ ማንነት መሰረት ነዉ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ሲናገር “ Oromummaan hundee Oromooti” ይላል፡፡ ኦሮሙማ በኦሮሞነት ማመን ነዉ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ኦሮሞ የሚያሰኙት የማንነቱ መገለጫዎች በጋራ እንዲጠቀም፣ ባህሉ እንዲያድግ ጥረት ማድረግ ማለት ነዉ፡፡ … ኦሮሙማ የኦሮሞን ታሪክ፣ ባህል፣ ፖለቲካ ፣ ቋንቋ ማወቅ እና መገንባት ማለት ነዉ፡፡ …
…ኦሮሙማ እንደ ርዕዮተ ዓለም የሰዉን ልጅ ነጻነት ማስከበር፣ የኦሮሞን የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ራዕይ እና የብዝሃ ብሄር ዴሞክራሲን የሚጨምር ነዉ፡፡ ኦሮሙማ … በኦሮሞ ማህበረሰብ ዉስጥ ሰዉ ልጆች እኩልነት ጥረት ማድረግ… የኦሮሞን ቋንቋ ማሳደግ፣ የሃይማኖት እኩልነትንና ሌሎችንም ልዩነቶች መቀበልና ማወቅን ያካትታል፡፡…. (ከገጽ 60-63)
መጽሃፉን ገዝታችሁ አንብቡት፣ በእጅጉ ታተርፉበታላችሁ!
Credit: Addisu Arega Kitessa
Comments
Post a Comment